የሀገር ውስጥ ዜና

በጉራጌ ዞን ከ57 ሚሊየን ብር በላይ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ

By Meseret Awoke

June 13, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከ57 ሚሊየን ብር በላይ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በጉራጌ ዞን ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከ24 ሚሊየን ብር በላይ የተገነባውን የመሀል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መርቀው ከፍተዋል።

የመሀል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2003 ዓ.ም ግንባታውን ለማካሄድ የመሠረት ድንጋይ መጣሉን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበትን የመሀል አምባ ኮንስትራክሽን እና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መርቀው ከፍተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!