ጠ/ሚ ዐቢይ ህብረተሰቡ በመጪው ሰኞ ድምጽ እንዲሰጥ ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምርጫና አረንጓዴ ዐሻራ እውን እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
“የዛሬ ሳምንት ኢትዮጵያውያን በ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ድምፃችንን እንሰጣለን፤ ይህ ምርጫ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሚሆን ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።
መላው ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበር ወደ ምርጫው በሚሄዱበት ወቅት ቀኑን የዜግነት ግዴታቸውን በመወጣት የትውልድ ማኅተም ለመተው እንዲጠቀሙበትም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “በመጪው ሰኞ ውጡና ድምጽ ስጡ፣ እንዲሁም አረንጓዴ ዐሻራችሁን አስቀምጡ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነው ቀኑን ታሪካዊ የዴሞክራሲ ቀን እንዲያደርግትም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!ጠ