Fana: At a Speed of Life!

ናፍታሊ ቤኔት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ቃለ መሃላ ፈፀሙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ናፍታሊ ቤኔት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ቃለ መሃላ ፈፅመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእስራኤል 13ኛው ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ነው ቃለ መሃላ የፈፀሙት፡፡
ያኢር ላፒድ ደግሞ ተለዋጭ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ተመርጠዋል፡፡
ናፍታሊ ቤኔት መንግስታቸው “ለሁሉም ህዝብ ጥቅም እንደሚሰራ” ገልፀው ትምህርትና ጤና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የቀድሞ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የተቃዋሚ ፓርቲው የሊኩይድ ፓርቲ መሪ ይሆናሉ፡፡
የያሚና ፓርቲ መሪ ቤኔት እስከ መስከረም 2023 ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ይቆያሉ ነው የተባለው፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.