የሀገር ውስጥ ዜና

በፀሐይ ታዳሽ ኃይል መሰማራት ከሚፈልጉ ኩባንያዎች ጋር የቅድመ ኢንቨስትመንት ውይይት ተካሄደ

By Tibebu Kebede

June 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፀሐይ ሃይል ልማት በጋራ ለመሰማራት ፍላጎት ካሳዩት ሁለት ኩባንያዎች ጋር በበይነ መረብ የቅድመ ኢንቨስትመንት ውይይት ተካሄደ፡፡

ኩባንያዎቹ ደብልዩ ኤስ ቢ እና ሶላር ስቶን ሲሆኑ፥ መቀመጫቸውን አሜሪካ ሚኔሶታ ያደረጉ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃፊዎች የተሳተፉ ሲሆን፥ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ እንዲሁም በዘርፉ ያለውን ሰፊ እድል በተመለከተ ገለጻ ሰጥተዋል።

የኩባንያዎቹ ሥራ ሃላፊዎች በበኩላቸው አስፈላጊውን ጥናት በማጠናቀቅ ወደ ተግባራዊ ምዕራፍ መሸጋገር እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

ኩባንያዎቹ ወደ ሥራ ሲገቡ ቢያንስ 100 ሜጋ ዋት የፀሐይ ታዳሽ ኃይል በሶማሌ ክልል ለማምረት ዕቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!