Fana: At a Speed of Life!

በ800 ሚሊየን ብር ወጪ ለሚገነባው የከሰል ድንጋይ ማምረቻ ፋብሪካ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ለሚገነባው የከሰል ድንጋይ ማምረቻ ፋብሪካ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

800 ሚሊየን ብር ወጪ የሚደረግበት ፋብሪካ በሰን ማይኒንግ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ የሚገነባ ሲሆን፥ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ከ1 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።

ግንባታው ሲጠናቀቅ በወር 800 ሺህ ቶን የድንጋይ ከሰል እንደሚያመርት ተገልጿል፡፡

የፋብሪካው መገንባት ለድንጋይ ከሰል የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ የመቀነስ አቅም ይኖረዋል ተብሏል።

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ፋብሪካው ለግዙፍ ኢንዱስትሪዎች የሃይል አማራጭ ትልቅ ግብአት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

ለአካባቢው ማህበረሰብም የስራ ዕድል እንደሚፈጥር በመጥቀስ፥ የአካባቢው ነዋሪ ፕሮጀክቱን በማገዝና የአካባቢውን የተፈጥሮ ሃብት በመጠበቅ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በርካታ የሰው ሃይልና የተፈጥሮ ሀብት እያለ በየአመቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማውጣት ምርት ከውጭ ማምጣት ትክክል አለመሆኑን አንስተዋል፡፡

አሁን እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ይህንን ጫና ለመቀነስ አንድ እርምጃ ተጉዘናል ብለዋል።

በቀጣይም ኢትዮጵያ ለድንጋይ ከሰል በዓመት የምታወጣውን ከ200 ሚሊየን በላይ ዶላር እና ከውጭ የምታስገባውን የብረት ምርት ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዘመን በየነ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.