የቡድን 7 አባል ሀገራት ተጨማሪ 1 ቢሊየን የኮቪድ ክትባት ለታዳጊ ሃገራት ለመለገስ ተስማሙ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡድን 7 አባል ሀገራት ተጨማሪ 1 ቢሊየን የኮቪድ19 ክትባት ለታዳጊ ሀገራት ለመለገስ ተስማሙ።
ለመለገስ የተስማሙት የክትባት መጠን በትናንትናው ዕለት ለመስጠት ከተስማሙት 1 ቢሊየን ክትባት በተጨማሪነት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡
አሜሪካ 500 ሺህ የፋይዘር ክትባት የምታቀርብ ሲሆን ክትባቱ ከሚቀጥለው ነሐሴ ወር ጀምሮ ይሰራጫል ተብሏል፡፡
ይህም ለ92 ታዳጊ ሃገራት የሚዳረስ መሆኑን የሲ ጂ ቲ ኤን ዘገባ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪነት የሚለገሰውን ክትባት ተከትሎም ቡድኑ ካለፈው የፈረንጆቹ አመት ጀምሮ የሚሰጠውን የክትባት መጠን ወደ 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ያደርሰዋል ነው የተባለው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!