የሀገር ውስጥ ዜና

የመከላከያ ጦር ኮሌጅ እና ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

By Tibebu Kebede

June 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ የጦር ኮሌጅ እና ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ኢትዮጵያ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

ሰነዱን የመከላከያ ጦር ኮሌጅ አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ሀብታሙ ጥላሁን እና የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ዋና ተጠሪ ኒኮላስ ቮን አርክ መፈራረማቸውን የኮሌጁ መረጃ ያመላክታል፡፡

ስምምነቱ የዓለም አቀፍ የሠብአዊ መብት ሕግና ተያያዥ የሠብአዊ መብት ድንጋጌዎች ኮሌጁ በሚሰጣቸው ስልጠናዎችና በሚያደርጋቸው ምርምሮች በተሻለ መንገድ እንዲካተቱና በኮሌጁ ሰልጣኞች ከፍ ያለ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!