Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድምና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ተከስቶ የነበረው ችግር መፈታቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድምና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በሚገኙ  የማህበረሰብ ክፍሎች የጥፋት ኃይሎች በፈጠሩት ሴራ የተፈጠረው መቃቃር መከላከያ ሠረዊቱ በማሸማገል ችግሩን መፍታት መቻሉ ተገለጸ።

ሠራዊቱ የሀገርን ሉዓላዊነት ወደ ማስከበር ተልዕኮው እንዲመለስ የውስጡን ችግር እኛው መፍታት አለብን ሲሉም የሀገር  ሽማግሌዎች ጥሪ አቅርበዋል።

በአጣየና አካባቢው የተፈጠረውን ሁከትና ብጥብጥ ለማስቆም ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራርና አባላት ከአርሶ አደሩ ጓሮ ድረስ በመሄድ የሕዝቦችን አንድነት ለማምጣት እየሠሩ  መሆኑ ተገልጿል።

ኢትዮጵያውያን ካላቸው አኩሪ እሴቶች አንዱ በባህላዊ መንገድ ግጭቶችን መፍታት ሲሆን÷ በአጣዬና አካባቢው የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት መከላከያ ሠራዊቱ በዛፍ ሥር ሕዝቦችን በማሰባሰብ ወደ ሠላም ድርድር አምጥቷል።

በአጣዬ የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ ÷ አሁን ላይ ኢትዮጵያን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች በየቀበሌው በመግባት አብሮነትን እና አንድነትን እያናጉ በመሆኑ ህዝቡ መንቃት አለበት ብለዋል።

በዕርቅ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የሀገር ሽማግሌዎች በበኩላቸው ÷መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳን ድንበር ወደማስጠበቅ ተልዕኮው እንዲመለስ ሁሉም ለሠላም ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአጣዬና አካባቢው ዳግም ግጭት እንዳይከሰት በሕዝቦች መካከል ቃለ መሐላ በማስፈፀም ሀገራዊ አደራውን እየተወጣ እንደሚገኝ ከመከላከያ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.