የሀገር ውስጥ ዜና

ቦርዱ ሰኔ 14 ቀን ድምጽ ባልተሰጠባቸው አካባቢዎች ጳጉሜን 1 ቀን ድምጽ እንደሚሰጥ አስታወቀ

By Tibebu Kebede

June 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ምክንያቶች ሰኔ 14 ቀን ድምጽ ባልተሰጠባቸው አካባቢዎች ጳጉሜን 1 ቀን 2013 ዓ.ም ድምጻቸውን እንደሚሰጡ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ እያከናወናቸው ያሉ የምርጫ ዝግጅቶችን እና የአስፈጻሚዎችን ስልጠና አስመልክቶ መግልጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውን የድምጽ መስጫ ወረቀት ከዛሬ ጀምሮ ወደተለያዩ የምርጫ ክልሎች እንደሚላክ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በዚህም በተለያዩ ምክንያቶች ድምጽ ባልተሰጠባቸው አካባቢዎች ጳጉሜን 1 ቀን ድምጽ እንደሚሰጥና ይህም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቀመጠውንና የምርጫ ሂደቱ በ2013 ዓ.ም መጠናቀቅ ይኖርበታል የሚለውን መመሪያ የተከተለ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከጳጉሜን 1 ቀን በኋላ ምንም አይነት የድምጽ መስጠት መርሃ ግብር እንደማይከናወንምን ነው የተገለጸው፡፡

በመግለጫው እስካሁን የቁሳቁስ በተለይም የስልጠና መስጫ ቁሳቁስ ማሰራጨት የተቻለ ሲሆን፥ ከዚህ ባለፈም በቀሩት ቀናት እና ባለፉት ቀናትም ዜጎች ድምጻቸውን እንዲሰጡ በእጅ ስልክ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ከመላክ አንስቶ የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውም ነው የተነሳው፡፡

በዚህም 102 የሲቪክ ማህበራት ዜጎች ድምጻቸውን እንዲሰጡ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ስለመሆናቸው ተጠቁሟል።

በመግለጫው ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔን ቀን መቼ ሊሆን እንደሚችል መረጃውን በቅርቡ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል ተብሏል።

መራጮች ድምጻቸውን በተገቢው መንገድ እና ነጻ ሆነው መሳተፍ እንዲችሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ተሳትፎ ወሳኝ ስለመሆኑም ተነስቷል።

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!