የሀገር ውስጥ ዜና

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2014 ረቂቀ በጀት ላይ ነገ ይወያያል

By Tibebu Kebede

June 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው የ2014 ረቂቅ በጀት ላይ በሚቀርብለት የበጀት መግለጫ ላይ ይወያያል።

ምክር ቤቱ በ6ኛ አመት 15ኛ መደበኛ ስብሰባው በረቂቅ አዋጁ ላይ በመወያየት የተለያዩ የውሳኔ ሃሳቦችን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የፌደራል መንግስት የ2014 በጀት አመት ረቂቅ በጀት ላይ የበጀት መግለጫ ለምክር ቤቱ የሚያቀርቡ ይሆናል።

ምክር ቤቱ በሚቀርብለት የበጀት መግለጫ ላይ ተወያይቶ ረቂቅ የበጀት አዋጁን ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራም ነው የሚጠበቀው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!