ስፓርት

በአውሮፓ ዋንጫ ስሎቫኪያ ድል ቀንቷታል

By Tibebu Kebede

June 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ምሽት ቀጥሎ ተካሂዷል፡፡

በምድብ 5 በተደረገ ጨዋታ ፖላንድ በስሎቫኪያ ተሸንፋለች፡፡

ጨዋታውን ስሎቫኪያ 2 ለ 1 ስታሸንፍ ወይቼች ሸዝኒ በራሱ መረብ እንዲሁም ስክሪኒዬር ለስሎቫኪያ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡

ሸዝኒም በውድድሩ ከክለብ አጋሩና የቱርኩ ተከላካይ ሜሪህ ዴሚራል ቀጥሎ ሁለተኛውን ጎል በራሱ መረብ ላይ አስቆጥሯል፡፡

ካሮል ሊኔቲ ደግሞ ለፖላንድ የማስተዛዘኛዋን ጎል አስቆጥሯል፡፡

ዓርብ የጀመረው ውድድር እስከ ፈረንጆቹ ሃምሌ 11 ድረስ ይቀጥላል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!