Fana: At a Speed of Life!

33ተኛው የምስራቅ ናይል ሃገራት የሚንስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 33ተኛው የምስራቅ ናይል ሃገራት የሚንስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በስብሰባው የናይል ተፋሰስን በጋራ ማልማት የሚቻልበት መንገድና እስካሁን በተፋሰሱ የተሰሩ ስራዎች የሚቃኙ ይሆናል።
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ናቸው።
ይህንኑ ስብሰባ ለመታደም የሱዳንና የደቡብ ሱዳን የውሃ ሚንስትሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻዎች ተገኝተዋል።
ግብጽ የዚህ ምክር ቤቱ አባል ብትሆንም በስብሰባው ሳትገኝ መቅረቷል ከውሃ ፣ መንሶና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.