Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ ከተማ ድምጽ በሌለው መሳሪያ ዘረፋ ሊፈጽሙ የነበሩ ዘጠኝ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በመቐለ ከተማ ድምጽ በሌለው መሳሪያ ዘረፋ ሊፈጽሙ የነበሩ ዘጠኝ ግለሰቦች በወጣቶች ትብብር በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በመቐለ  ሰሜን ክፍለ ከተማ ከለሊቱ ስድስት ሰአት መናኻሪያ አካባቢ ነው።

በአንድ ቡድን የተደራጁት ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ቤት ለመዝረፍ የሚያስችል እና ግለሰቦች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ስለታማ ፣ድምጽ አልባ መሳሪያ ይዘው ዘረፋውን ሊፍጽሙ ሲሉ ስድስት አባላት ያለው የወጣቶች ቡድን ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ምርመራ እየተደረገባቸው  ሲሆን÷ የከተማ ወጣቶችን በማስተባበር ጸጥታን የማስጠበቅ ስራው ውጤት ማሳያ ነው ተብሏል።

በመቀለ በየክፍለ ከተሞቹ እስከ 250 የሚደርሱ ወጣቶችን መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠና በመስጠት እንዲደራጁ ተደርጓል።

በየቀጠናቸው አስር አስር ወጣቶች ከአስተዳደሩ በተሰጣቸው መለያ ወይም ባጅ ከጸጥታ ሀይሉ ጋር በመሆን አከባቢያቸውን እንዲጠብቁ እየተደረገ ነው።

የመቀለ ዞን ጊዜያዊ አስተዳደር ጸጥታና ደህንነት ዘርፍ ሀላፊ ገብረሚካኤል ሓየሎም÷ የከተማዋን ጸጥታ በተሻለ ለማረጋጋት ከፌደራል፣ ክልልና ከተማ ድረስ የተቀናጀ ስራ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ጥናት ተጠናቆ ተግባራዊ ወደ ማድረግ እየተገባ ነው ብለዋል።

አሰራሩ ክፍለ ከተሞችንም ያካተት በመሆኑ እስከታች ድረስ ቅንጅታዊ ስራን ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።

የከተማ የፖሊስ አባላት ተጨማሪ የአቅም ግንባታ እና ግብአቶች ያስፈልጉታል ብለዋል።

መደበኛ ፖሊሶች አካባቢ ድሮም አልፎ አልፎ ከስራ መጥፉት የሚያጋጥም ችግር  መሆኑን ገልጸው÷ ሰሞኑን ከአባላቱ የጠፉ እንዳሉ አስታውሰዋል።

የጠፉ የተወሰኑ አባላት የት እንደገቡ እስካሁን ማረጋገጫ አልተገኘም ያሉት ሀላፊው ክትትል እየተደረገባቸው መሆንንም ገልጸዋል።

በመቐለ  በማረቢያ ቤት የነበሩ እስረኞች እንዲለቀቁ ከተደረገ በኋላ ዳግም በወንጀል እየተሳተፉ እንደሆነ የተደረሰበት ሲሄን በቅርቡ ማረሚያ ቤቱ ሲከፈት በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ በሙሉ አቅም ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

በኃይለየሱስ ስዩም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.