ሁሌም ቢሆን የህዝብን የልብ ትርታ ማድመጥ ያስፈልጋል – ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ከአይዲያ ኢንተርናሽናል ከተሰኘ ግብረ ሰናይድርጅት ጋር በመተባበር በመላው ሀገሪቱ ያስጠናውን ጥናት፣ ለሲቪክ ሶሳይቲ፣ ለተፎካካሪ ፖርቲዎች፣ ለሚዲያ አካላት እና ለሌሎች ለባለድርሻ አካላት እያቀረበ ይገኛል።
በፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል÷ የዚህ ጥናት ዓላማ ህዝብ በፖለቲካ ፣በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን ሃሳብ አድምጦ ተገባውን ምላሽ ለመስጠት ነው ብለዋል።
ሁሌም ቢሆን የህዝብን የልብ ትርታ ማድመጥ ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትሯ ÷ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የሚገኙ ባህላዊ እሴቶቻችንና ማህበራዊ ሃብቶችን ለሰላም ግንባታ ስራዎች መሰረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
እንደዚህ አይነት ጥናቶች እውነተኛ የህዝብ ፍላጎትና ትርታ ለማዳመጥ እና ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ያግዛል ተብሏል።
በጥናቱ በመላው ሀገሪቱ የተወጣጡ ከ25ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል።
በጥናቱ በየአካባቢው ያሉ ፓለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ችግሮች ተለይተዋል።
የሰላም የሚኒስትር አማካሪ ዶክተር አብዲ ዘነበ በቀረበው ጥናት ላይ ትንታኔና ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን÷ ተሳታፊዎም የተለያዩ ሃሳቦችን እየሰጡ እንደሚገኙ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!