Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ኔቶ ወታደራዊ ስጋት እየሆነች ነው በሚል ያቀረበባትን  ውንጀላ ውድቅ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ለዓለም ሀገራት ወታደራዊ ስጋት እየሆነች ነው በሚል ያቀረበባትን  ውንጀላ ውድቅ አድርጋለች፡፡

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) መሪዎች በብራሰልስ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም  ቻይና ኒውክሌርን  ጨምሮ ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን በፍጥነት በማምረት  ወታደራዊ አቅሟን  እያሳደገች መሆኑን የቡድኑ መሪዎቸ  ኮንነዋል፡፡

ቤጂንግ በምታበለጽጋቸው ጦር መሳሪያዎቸ ዙሪያ ግልጽ አለመሆኗን ያነሱት መሪዎቹ፣በተለይም ከሩሲያ ጋር የጀመረችው ወታደራዊ ትብብር ስጋቱን ይበልጥ ያንረዋል  ነው ያሉት፡፡

ቻይና በበኩሏ የኔቶ አባል ሀገራት የቤጂንግ  ወታደራዊ አቅም ለዓለም ስጋት እየሆነ  ነው በሚል ያቀረቡትን ስጋት መሰረት ቢስ ውንጀላ ስትል አጣጥላለች፡፡

ቤጂንግ  ወታደራዊ አቅሟን ለማዘመን  ግልጽ እና ምክንያታዊ የሆኑ አዳዲስ እንዲሁም  ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀሟን አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጣለች፡፡

ይሁን እንጂ  ለየትኛው ሀገር  ስልታዊ  እንቅፋትም ሆነ ወታደራዊ ስጋት የመሆን እቅድ እንደሌላት ነው ቤጂንግ ያስታወቀችው፡፡

የቡድኑ አባል ሀገራት  ቻይና የዓለም ሀገራ ስጋት እየሆነች ነው በሚል የሚራምዱትን የተሳሳተ እና የተዛባ መላምት እንዲያቆሙም አስጠንቅቃለች፡፡

ምንጭ፡- ሬውተርስ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.