ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልምዷን ለጎረቤት ሀገራት እንዲያካፍሉ ከአምባሳደሮች ጋር ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በጎረቤት ሀገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያን ከሚወክሉ አምባሳደሮች ጋር በበይነ መረብ ተወያይተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት 1 ቢሊየን ችግኝ ማዘጋጀቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
በውይይቱ አቶ ደመቀ መርሃ ግብሩ በአከባቢ ጥበቃ፣ አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመግንባት መልካም ግንኙነት በአከባቢው እና በቀጠናው እንደሚፈጥር ታምኖበታል ብለዋል፡፡
እንዲሁም የልምድ ልውውጡ ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ትብብር እና ከመንግስታት ጋር ለመቀራረብ ጠቀሜታ አለው ነው ያሉት፡፡
ለፕሮጀክቱ መሳካትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ እንደሚሆኑ መገለፁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በጎረቤት ሀገራት በሚደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፣የዲያስፖራ ማህበረሰብ እና ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!