Fana: At a Speed of Life!

የፖለቲካ ፓርቲዎች የመጨረሻ የምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ቦታዎች ለትራፊክ ዝግ መሆናቸውን ፖሊስ ስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚደርጉትን የመጨረሻ የምርጫ ቅስቀሳ ምክንያት በማድረግ በከተማዋ አንዳንድ ቦታዎች ለተወሰነ ሰዓት መንገዶች ለትራፊክ ዝግ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያደርጉትን የምርጫ ቅስቀሳ በዛሬው እለት ሰኔ 9 ቀን 2013 ዓ.ም ያጠቃልላሉ ፡፡
ሰኔ 9፣ 2013 ዓ.ም የሚደረገውን የመጨረሻ ቀን የፓለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳን ምክንያት በማድረግ በፒያሳ አራዳ ህንፃ አካባቢ ከረፋዱ 5 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት፤ ከፒያሳ አራዳ ህንፃ ወደ ደጎል አደባባይ ፤ከአራዳ ህንፃ ወደ ሚኒልክ አደባባይ ፤ መዘጋጃ ቤት እስከ አቡነ ጼጥሮስ አደባባይ እንዲሁም መስቀል አደባባይ ዙሪያውን ከጠዋቱ 12፤00 እስከ 3 :00ሰዓት ድረስ ለጊዜዉ ለትራፊክ ዝግ መሆኑን አሽከርካሪዎች በመረዳት ሌሎች አማርጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች ላይ በሚያደርጉት የምርጫ ቅስቀሳ በብዙ ቦታዎች ላይ የትራፊክ መጨናነቅ ተከስቶ በከተማችን ነዋሪዎች ላይ ልዩ ልዩ መጉላላቶች ቢከሰትም ፤የምርጫ ፕሮግራም በአምስት ዓመት አንድ ጊዜ የሚከወን መሆኑን በመረዳት ህብረተሰቡ ላሳየው ቀና ትብብር የአዲሰ አበባ ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.