Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ከተማ በ300 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ዛሬ ይመረቃሉ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ በ300 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክት ዛሬ ይመረቃሉ።

በከተማው በ2013 ዓ.ም አስራ አምስት አዳዲስና ሰባት ነባር በአጠቃላይ 22 ፕሮጀክቶችን ሰርቶ ለማጠናቅ ተቅዶ 21ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለምርቃት ዝግጁ መሆናቸውን የጅማ ከተማ አስተዳደሩ ገልፆል።

ፕሮጀክቶቹም የመጠጥ ውሃ ማስፋፊያ፣የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ፣የገቢያ ማዕከል እና የአዌቱ የወንዝ ዳርቻ የልማት ፕሮጀክቶች ናቸው።

የአዌቱ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በአንጠቃላይ 1 ኪ.ሜ እርዝማኔ ያለው ሲሆን ከስታዲየም አንስቶ እስከ በቾ ድልድይና ከበቾ ድልድይ እስከ ቢሺሼ ድልድይ የማስዋብ ስራ ተጠናቆ ዛሬ ይመረቃል።

ወንዙ ከዚህ ቀደም ሞልቶ የአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ጉዳት እያደረሰ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ፕሮጀክቱ ይህን ችግር ከመቅረፍ ባለፈ ለከተማዋ ውበት እንደሚሆንና ለወጣቶችም የስራ እንደሚፈጥር ተነግሮለታል።

ዛሬ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ፕሮጀክቶች ይመረቃሉ።

በሙክታር ጣሃ እና ተመስገን አለባቸው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.