አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ለፀጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጡ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልክዕተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ መደበኛ ባልሆነ ስብሰባ ላይ ለፀጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጡ፡፡
አምባሳደር ታዬ በዚህ ወቅት መንግስት በክልሉ ያለውን ሰብአዊ ሁኔታ ማሻሻል ያለውን ቁርጠኝነት በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በክልሉ እየተደረገ ስላለው የሰብአዊ ድጋፍ ሁኔታ ማብራሪያ መስጠታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም በክልሉ ተፈጽሟል ከተባው የሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር ተያይዞ እየተደረገ ባለው ምርመራ ዙሪያም ገልጸዋል፡፡