የሀገር ውስጥ ዜና

በባህር ዳር እና ጅማ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅስቀሳ መዝጊያ ተካሄደ

By Meseret Awoke

June 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር እና በጅማ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅስቀሳ መዝጊያ ተካሄደ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጅማ ስታዲየም በመገኘት ለብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በመዝጊያ መርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም ህዝቡን ይዘን ኢትዮጵያን እናሻግራለን ብለዋል፡፡

“አሁን የኢትዮጵያን አንድነት አረጋግጠን ትኩረታችን የአፍሪካን ቀንድ የአፍሪካ ክንድ ማድረግ ነውም” ብለዋል በንግግራቸው።

በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ባለው የብልጽግና ፓርቲ ቅስቀሳ መዝጊያ መርሃ ግብር ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልሉ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊ የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

በሙክታር ጠሃ፤ ተጨማሪ መረጃ ከአሚኮ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!