የሀገር ውስጥ ዜና

ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉት አራት ቀናት የጥሞና ወቅት ይባላሉ- ምርጫ ቦርድ

By Meseret Awoke

June 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ የምርጫ ዑደት መመሪያ መሠረት ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉትን አራት ቀናት እንደሚያካትት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ፡፡

የጥሞና ወቅት በቅድመ የምርጫ ዑደት ውስጥ የሚገኝ ጊዜ ሲሆን፥ በዚህ ወቅትም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት፥ ማለትም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ሊተገብሯቸው የሚገቡ ሀላፊነቶች መኖራቸውን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች

• የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎችና ደጋፊዎቻቸው ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚየካሂዱት የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ ድምጽ መስጠት ከመጀመሩ ከአራት ቀን በፊት መጠናቀቅ አለበት፡፡

• የፓለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው አራት ቀን ሲቀረው ማንኛውም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡ (በኢንተርኔት፣ በማህበራዊ ሚዲያ፣ በግንባር፣ ቤት ለቤት፣ በአደባባይ ፣ በአዳራሽ ስብሰባ ምንም አይነት ቅስቀሳ ማከናወን በጥብቅ የተከለከለ ነው)

• የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት እንዲሁም ቃለ-መጠይቆችን ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡

• ብሄራዊ የምረጫ ቦርድ የሚያወጣቸውንም መመሪዎች ሊፈጽሙ ይገባል፡፡

ለመገናኛ ብዙሀን ተቋማት

• የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት በጥሞና ወቅት ማንኛውንም ምርጫ ተኮር እንቅስቃሴዎችን ማሰራጨት አይፈቀድላቸውም፡፡

በተጨማሪም የፓለቲካ ፓርቲ እጩዎችን አግኝተው ቃለ መጠይቆችን መስራት አይፈቀድላቸውም፡፡

• የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሚወጡ መረጃዎችን የማስተጋባት ሀላፊነት ሲኖርባቸው ከዚህ ውጪ በመመሪያዎች ላይ ያልተደነገጉ ተግባራትነ እንዲፈጽሙ አይፈቀድላቸውም፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!