የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት በአማራ ክልል በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ሊሰጥ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የግዕዝ ቋንቋን በመደበኛው ትምህርት ውስጥ እንደ አንድ የትምህርት አይነት በቀጣዩ የትምህርት ዘመን በተመረጡ ትምህርት ቤቶች መስጠት እንደሚጀምር የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው ግዕዝን በመደበኛ ትምህርትነት ለማስጀመር የሚያስችል የውይይት መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሂዷል።
የኢትዮጵያን የመካከለኛው ዘመን ታሪክ ለማወቅና ሀገር በቀል እውቀቶችን በአግባቡ ተጠቅሞ ሀገራዊ እድገትን ለማረጋገጥ የግዕዝ ቋንቋ በትውልዱ በስፋት እንዲታወቅ ማድረግ እንደሚገባ መገለጹን የዘገበው ኢቢሲ ነው።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ይልቃል ከፍአለ ግዕዝን ከእኛ ከባለቤቶቹ ይልቅ የተለያዩ የውጭ ሀገራት እስከ 3ኛ ዲግሪ ድረስ በማስተማር በአግባቡ አጥንተው ተገልግለውበታል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ብዙዎቹ ቀደምት መፅሐፍት በግዕዝ የተፃፉ እንደመሆናቸው ቋንቋውን ማወቅ የኢትዮጵያን የቆየ ጥበብ ለመጠቀም ያስችላልም ብለዋል።
ወደፊትም ከግዕዝ በተጨማሪ የአረብኛ ቋንቋን በጥናት ላይ ተመስርቶ በተመረጡ የክፍል ደረጃዎች እንዲሰጥ ይደረጋልም ተብሏል።
ይህም ብዝሀ ልሳን የሆነ ማህበረሰብ በመፍጠር በየትኛውም አካባቢ ተግባብቶ ለመስራት እገዛው የጎላ መሆኑ ተገልጿል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!