Fana: At a Speed of Life!

በአርሲ ዞን 354 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም ይለማል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርሲ ዞን በመኸር እርሻ 354 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም እርሻ እንደሚለማ የዞኑ ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

590 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 354 ሺህ ሄክታሩ በክላስተር የሚለማው ተብሏል፡፡

ለዚህም ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የአርሲ ዞን ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

233 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር፣ 615 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች የቀረበ ሲሆን፥ አጠቃላይ 924 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ለማቅረብ ተይዞ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

የዞኑ አርሶ አደሮች በቴክኖሎጂ ታግዘው ወደ ዘመናዊ እርሻ እንዲሻገሩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ሃላፊው አስረድተዋል፡፡

በሚደቅሳ ቀቻ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.