Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ ዩኔስኮ ጽህፈት ቤት አዲስ አሰራር ሊዘረጋ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ዩኔስኮ ጽህፈት ቤት ስራዎችንና ግንኙነትን የሚያሳልጥ አዲስ አሰራር ሊዘረጋ ነው።

ውይይቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ ጽህፈት ቤት የኮሚቴ አባላትና ተወካዮች በተገኙበት በትምህርት ሚኒስቴር ሰብሳቢነት ነው የተካሄደው፡፡

በመድረኩም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ ጽህፈት ቤት እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን እና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ ጽህፈት ቤት ያለፈውን በማረም የወደፊቱን በማ

ብሔራዊ ዩኔስኮ ጽህፈት ቤቱ በሁሉም አባል መስሪያ ቤቶች፣ የተሰሩ ስራዎችን በቀላሉ ለማግኘት፣ለመጫን እንዲሁም በፓሪስ ከሚገኘው የዩኔስኮ ዋና ጽህፈት ቤት ጋር ለመገናኘት የሚያስችል አዲስ ፕላትፎርም በአጭር ጊዜ ይዘረጋል ብለዋል፡፡

በፓሪስ የኢፌዴሪ ሚሲዮን ባለሙሉ ስልጣን ሚኒስትር የስራ ደረጃ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርት እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ምክትል ቋሚ መልእክተኛ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ ጽህፈት ቤት ሰብሳቢነት በአዋጅ የተሰጠው ትምህርት ሚኒስቴር አደረጃጀቱን ማጠናከር ይገባዋል ብለዋል፡፡

በብሔራዊ ዩኔስኮ ጽህፈት ቤቱ እስካሁን በጋራ ባለመሰራቱ ምክንያት የተሰራውም ስራ የተበታተነ እንዲሁም ሚዛን የሚደፋ አለመሆኑን ጠቅሰው፥ ይህንን ከመሰረቱ መፍታት ይገባል ስለመባሉ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.