የሀገር ውስጥ ዜና

በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የበይነ መረብ ውይይት አካሄደ

By Meseret Awoke

June 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ኡጋንዳ ካምፓላ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አስተባባሪ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ውይይት አካሂዷል፡፡

የበይነ መረብ ውይይቱም የሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት አስመልክቶ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከውይይቱ ጎን ለጎን የግድቡን ግንባታ ለመደገፍ በተካሄደው የቦንድ ሽያጭ 21ሺህ 420 ዶላር ገቢ ተሰብስቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!