Fana: At a Speed of Life!

በአጣዬና አካባቢው የተፈጠረውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የእርቀ ሰላም ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአጣዬና አካባቢው የተፈጠረውን ችግር በዘላቂነት መፍታት የሚያስችል የእርቀ ሰላም ሥነ- ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጭሬ በተባለ ቦታ እየተካሄደ ባለው የእርቅ ሰላም ሥነ-ሥርዓ ከአርጡማ ፉርሲ፣ አንፆኪያ ገምዛ እና ማጀቴ አካባቢዎች ያሉ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

በአካባቢው የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል ደስታ አብቼ እንደገለጹት፥ ከአሁን በፊት አራት ተከታታይ የእርቅ መርኃግብሮች ተካሂደዋል፡፡

አሁንም ለተከታታይ ቀናት የእርቅ መርሃ ግብሮች በተለያዩ ቦታዎች እንደሚደረጉም ነው የገለጹት፡፡

ከአካባቢው የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች መደረጋቸውን ያነሱት አስተባባሪው፥ የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ወደ ነበረ ቀያቸው ለመመለስ የሚደረገው ጥረትም ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

የተዘጉ መንገዶችን የማስከፈት እና ጸረ-ሰላም ኃይሎች የሚነዙትን የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በማክሸፍ ዜጎች ዘላቂ ሰላም የሚያገኙበትን ሁኔታ ለመቀየስ እየተሠራ እንደሆነ መግለፃቸውንም አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.