Fana: At a Speed of Life!

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 4 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በአክሱም፣ ዓድዋና እና ሽረ ከተሞች ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ነው ድጋፉን ያደረገው፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው ዜጎችም 6 ሺህ 17 የሚደርሱ አራስና የሚያጠቡ እናቶች ሲሆኑ፥ አሁን ላይም በከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተጠለሉ መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከተደረገው 4 ሚሊየን ብር ቁሳቁስ እርዳታ በተጨማሪም 5 ሺህ 825 ፍራሾች ለተፈናቃዮች ተሰጥተዋል፡፡

በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና የአደጋ ጊዜ አስቸኳይ ምላሽ ግብረ-ኃይል ያስታወቀው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.