Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሉሊት ከሩዋንዳ ፖሊቴክኒክ ምክትል ቻንስለር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሩዋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሉሊት ዘውዴ ከሩዋንዳ ፖሊ ቴክኒክ ምክትል ቻንስለር ዶክተር ጄምስ ጋሹምባ፣ ከአካዳሚክ ጥናትና ተቋማዊ ልማት ምክትል ኃላፊ ዶክተር ሲልቪ ሙሲዮ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ የፖሊ ቴክኒክ አመራሮቹ ኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የካበተ ልምድ እንዳላት ገልጸዋል፡፡

ተቋማቸው በዋነኛነት በሎጅሰቲክና ትራንሰፖርት ፣ በኤርፖርትና አየር መንገድ አስተዳደርና በምድር ባቡር ዙርያ ልምድ ለመቅሰምና በቀጣይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠርና በትብብር ለመሰራት ያላቸውን ፍላጎትም ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር ሉሊት በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አገር በቀል የቴክኒክና ሙያ ሥራዎች ከፍተኛ ልምድ እንዳላት፣ አገር በቀል ክህሎቶችና እውቀቶች ዘመኑ የሚጠይቀውን ዕድገት ጋር በማዘመን፣ በስርዓተ ትምህርት በማካተትና ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር ፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፖሊሲና ሰትራቴጂ በመቅረጽና በማስፋፋት በርካታ የሰለጠነ የሰው ሀይል በማፍራት ለኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አብራርተውላቸዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ በሚገኙ ወደ 1ሺህ በሚሆኑ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኮሌጆች ውስጥ የሚሰጡትን በርካታ የትምህርት ዓይነቶችን በዝርዝር መግለጻቸውን በሩዋንዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሩዋንዳ ፖሊ ቴክኒክና በኢትዮጵያ የሚመለከታቸው አካላት መካከል ግንኙነቱ እንዲፈጠር ኤምባሲው ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች አምባሳደሯ አረጋግጠውላቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.