Fana: At a Speed of Life!

በኮንሶ ዞን ለብልጽግና ፓርቲ የማጠቃለያ የድጋፍ ሰልፍና ምርጫ ቅስቀሳ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ለብልጽግና ፓርቲ የማጠቃለያ የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ እና የዞኑን አመራሮች ጨምሮ በዞኑ ስር ካሉ ሶስት ወረዳዎችና አንድ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ተሳትፈዋል።

በድጋፍ ሰልፉ የውጭ ጣልቃ ገብነት ይቁም፤ ኢትዮጵያ ሉዓላዊት ሃገር ናት፤ አባይ በኢትዮጵያውያን ይገነባል እና በአባይ ጉዳይ አንደራደርም የሚሉ መፈክሮች ተደምጠዋል።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳውድ ገበየሁ ÷ ብልጽግና ፓርቲ በብዙ ችግሮች ውስጥ ያለፈና በተለያዩ የልማት ዘርፎች ላይ ውጤቶችን ያስመዘገበ ፓርቲ መሆኑን ገልፀዋል።

ፓርቲው ለዜጎች እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ተግቶ ይሰራል ያሉት አስተዳዳሪው ÷ ከለውጡ በኋላ ባሉ ጉዞዎችም ይህንን ማሳየት መቻሉን አውስተዋል።

ብልጽግና ፓርቲ በሚሰራቸው ሁሉን አካታች ስራዎችም ሁሉንም ዜጋ እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል ነው ያሉት።

ብልጽግና በህዝብ ድምፅ ምርጫውን የሚያሸንፍ ከሆነም የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው አቶ ዳውድ የገለጹት፡፡

የሰልፉ ተሳታፊዎችም ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሃላፊነት እንደሚወጡ በድጋፍ ሰልፉ ወቅት ተናግረዋል፡፡

በትዝታ ደሳለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.