በግለሰቦችና ቡድኖች እየተፈጸመ ያለውን የግድያና ዝርፊያ ወንጀል ለመከላከል እየተሰራ ነው – የትግራይ ክልል ጸጥታ ቢሮ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በግለሰቦችና ቡድኖች የሚፈጸም በጦር መሳሪያ የታገዘ የግድያና ዝርፊያ ወንጀል ለመከላከል የህግ ማስከበር ስራ እየተካሄደ መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር የማነ ገሰሰ እንደገለጹት ÷ በክልሉ ከህግ ማስከበር ዘመቻው በፊት በማረሚያ ቤት የነበሩ ከ10 ሺህ በላይ
ታራሚዎች ያለአግባብ አምልጠው ወጥተዋል።
በክልሉ የታራሚዎች አምልጦ መውጣትን ተከተሎ በግልና በቡድን በተደራጁ አካላት በጦር መሳሪያ የታገዘ የግድያና የዝርፊያ ወንጀል እየተፈጸመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በግለሰቦችና ቡድኖች እየተፈጸመ ባለው ወንጀል ህዝቡ ለሽብር መዳረጉን የጠቆሙት ረዳት ኮሚሽነር የማነ ÷ ወንጀሉን ለመከላከል የህግ ማስከበር ስራ እየተከናወነ መሆኑን አንተዋል፡፡
በተጀመረው የህግ ማስከበር ስራ በወንጀል የተሳተፉ ሰዎች በራሳቸው ተነሳሽነትና ጸጥታ ሃይሉ እየተወሰደ ባለው እርምጃ በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
ወንጀልን ለመከላከል እየተከናወነ ላለው የህግ ማስከበር ስራ ስኬታማነት የጸጥታ መዋቅሩን በሰው ሀይል፣ በቁሳቁስና በስልጠና የማጠናከር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ለሰባት ወር ስራውን አቋርጦ የነበረው የመቐለ ማረሚያ ቤትን ስራ ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።
ወንጀልን ለመከላከል የሚደረግ የህግ ማስከበር ስራ በጸጥታ አካሉ ብቻ ሊፈጸም የሚችል ባለመሆኑ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!