የሀገር ውስጥ ዜና

ስምንት ኪሎ ግራም ካናቢስ እፅ እና ሰባት ሺህ ኪሎ ግራም የኮንትሮባንድ ቡና ተያዘ

By Meseret Awoke

June 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰባት ሺህ ኪሎ ግራም ቡናና ስምንት ኪሎ ግራም የካናቢስ እፅ በሻሸመኔ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ተያዘ፡፡

የሰሌዳ ቁጥሩ አ.አ 36162 የሆነ አይሱዙ የጭነት መኪና መነሻውን ወላይታ ሶዶ ከተማ አድርጎ ወደ አ.አ በመጓዝ ላይ እያለ ከለሊቱ 6 ሰአት በሻሸመኔ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ መያዝ መቻሉን በጉምሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የህግ ተገዥነት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ኢዴሳ ለማ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቀዋል።

ተሽከርካሪውን ሙዝና ኮባ የጫነ በማስመሰል ከስር ግምቱ 840 ሺህ ብር የሆነ ኮትሮባንድ ቡና ጭኖ መገኘቱን ነው የሻሸመኔ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስተባባሪ ኢንስፔክተር አሰፋ የነገሩን።

በተመሳሳይ መነሻውን ሻሸመኔ አድርጎዳ ወደ መሀል ሀገር ሲጋዝ የነበረ ኮሮላ ዴክስ የቤት መኪና ውስጥ 8 ኪሎ ግራም የካናቢስ ዕፅ ትላንት ምሽት ሁለት ሰአት በመቆጣጠሪያ ጣቢያው ተይዟል፡፡

ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ እየረቀቀና እጨመረ የመጣውን የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር እንዲያመች ዘመናዊ መፈተሻ መሳሪያ በሻሸመኔና ጪጩ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን ከአቶ ኢዴሳ ለማ ሰምተናል።

በመቅደስ አስፋው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!