የሀገር ውስጥ ዜና

የስልጤ ዞን ማህበረሰብ ለሴቶች የሚሰጠውን የጊስትነት ማእረግ ከ500 ዓመት በኋላ ለወ/ሮ ሙፈርያት ከሚል ሰጠ

By Meseret Awoke

June 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የስልጤ ዞን ማህበረሰብ ለሴት ልጅ የሚሰጠውን የመጨረሻውን “የጊስቲነት” ማዕረግ ከ 500 ዓመታት በኋላ ለወይዘሮ ሙፈርያት ከሚል ሰጥቷል፡፡

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ከሚል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክትም፥ ባህላዊ እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ብሎም ለሀገር ግንባታ ትልቅ ትርጉምና ጠቀሜታ አላቸው ብለዋል።

በተጨማሪም ሚኒስትሯ፥ ‘‘ ላልተገደበው ፍቅራችሁና አክብሮታችሁ እጅግ አመሰግናለሁ’’ ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!