የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ከቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ላይ በሰራችው ስራ በ2021 በቴክኖሎጂ ቀዳሚ ከሆኑ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተተች

By Meseret Demissu

June 17, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ላይ በሰራችው ስራ በ2021 በቴክኖሎጂ ቀዳሚ ከሆኑ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተተች።

በኢኖቬሽን ዘርፍ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እየሰራች ያለችው ኢትዮጵያ ቆሻሻን ወደ ኤሌክትሪክ ሃይል በመቀየርና ፈጠራ በታከለበት የከተማ ፓርክ ልማት ስራዋ በዚህ ዝርዝር ውስጥ እንድትካተት እንዳደረጋትም ነው የተገለጸው።

የአለም ኢኮኖሚ ፎረም ባወጣው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ፣ ዚምባብዌ፣ የተባበሩት አረብ ኢሜሬትስና ኤልሳልቫዶር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በዚህ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት።

በዚህ አመት በወጣው መረጃ መሰረት ከተመረጡት ኩባንያዎች ውስጥ 30 ከመቶዎቹ እየተመሩ ያሉት ደግሞ በሴቶች ነው ተብሏል።

ዚምባብዌ በማንነት አስተዳደር ቴክኖሎጂ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የመካከላኛው ምስራቅ የባሉበት የፋይናንስ ትምህርት፣ ኤልሳቫዶር ደግሞ የባለ ብዙ የሁልጊዜ የምርትና አገልግሎት ገበያ ቦታ ላይ በሰሩት ስራ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ100 ዝርዝር ውስጥ ተካትተዋል።

በዚህ አመት ከወጣው ዝርዝር ውስጥ አሜሪካ በበርካታ አዳዲስ ስራዎች ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች።

የመረጃ መረብ ደህንነት፣ የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ፣ በጤናና የገንዘብ ተቋማት ላይ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የተዘረጉ የሰው ሰራሽ አስትውሎ ስራዎች፣ የቴክኖሎጂ የፋይናንስ ተቋማት፣ የአረንጓዴ ልማት ቀዳሚ መመዘኛዎችመደረጉን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒሰቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!