የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ጥሪ አቀረበ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ብዙ አሳሳቢ ጉዳዮች ባሉበት የሚካሄድ በመሆኑ ሁሉም አካላት ጠብ አጫሪ ከሆኑ ድርጊቶችና ንግግሮች እንዲቆጠቡና ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን ኢትዮጵያውያን በተለይ ወጣቱ የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።
የምርጫው ውጤት በሚመለከተው አካል እስኪገለጽ ድረስም ሁሉም በትዕግስት ሊጠባበቅ እንደሚገባም ገልጸዋል።
ምርጫውን የሚያስተባብሩ አካላትም የምርጫውን ሂደት በፍጹም ግልጸኝነት እንድያስተባብሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በዘመን በየነ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!