Fana: At a Speed of Life!

የሪፐብሊካን ጥበቃ ሃይል ለአቅመ ደካማ አረጋውያን የሚሆን የቤት ግንባታ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሪፐብሊካን ጥበቃ ሃይል በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ለአቅመ ደካማ አረጋውያን የሚሆን የቤት ግንባታ ጀመረ፡፡
ግንባታውን ያስጀመሩት የሪፐብሊካን ጥበቃ ሃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ብርሃኑ በቀለ የመከላከያ ስራዊቱ የተሰጠውን ህገ መንግስታዊ ተልዕኮ ከመወጣት እና የሃገርን ሰላም ከመስጠበቅ ጎን ለጎን፤በልማት ስራዎችም ላይ በትጋት ከመሳተፍ ባለፈ የተቸገሩ ወገኖቹን በመርዳት የበኩሉን ሚና እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡
እንዲሁም በማንኛውም ጊዜና ሰአት በሃገራችን እና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለመናድ የሚመጣ ሃይል ካለ በአስተማማኝ ሁኔታ እየመከትን የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ በማስቀጠል ህዝባዊነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል ፡፡
የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሃና የሺንጉስ በበኩላቸው የሪፐብሊኩ የጥበቃ ሃይል በተለያየ ጊዜያት ከክፍለ ከተማው ጎን በመሆን ህዝባዊ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ አስታወሰዋል፡፡
አሁንም በክፍለ ከተማው ወረዳ 8 ለሚገኙ አቅመ ደካማ አረጋውያንን ቤቶችን ሰርቶ ለመስጠት መርሃ ግብሩን መጀመሩ ከምንም በላይ የሚያስመሰግንና ህዝባዊነቱን ያስመረከረበት መልካም ተግባር ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.