Fana: At a Speed of Life!

የሞጆ ሁለገብ ሎጅስቲክስ ማዕከል ግንባታ የሲቪል ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞጆ ሁለገብ ሎጅስቲክስ ማዕከል ግንባታ የሲቪል ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

በመርሃ ግብሩ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የሞጆ ሁለገብ ሎጅስቲክስ ማዕከል የሀገሪቱን የወጪና ገቢ ጭነት በተሟላ መልኩ በማስተናገድ የኢትዮ -ጅቡቲ ኮሪደር ሎጅስቲክስን በማሳለጥ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል፡፡

በሲቪል ስራው ስድስት መጋዘኖች፣መንገዶችና የመንገድ ስራዎች፣ የውሃ፣ እሳት አደጋ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የኦኘሬሽን ፋሲሊቲዎች፣የኤሌክትሪክ ስርዓቶችና መሳሪያዎች፣አጠቃላይ እቃዎችና ቢሮዎች እንዲሁም ሕንጻዎችን ያካተተ ግንባታ የሚከናወን ይሆናል፡፡

የሲቪል ስራውን ሲሲኢሲሲ የተሰኘው የቻይና ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኩባንያ የሚያከናውነው መሆኑን ከኢትዮጵያ ማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.