የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢኒስቲቲዩት በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲቲዩት በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡
ስምምነቱ ቀጣይነት ያለው እና ውጤታማ የሆነ የአቅም ግንባታና የሥራ አመራር ሥልጠና መስጠትን አላማው ያደረገ መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሥራት ተቋማቱ ለሃገር የሚጠቅሙ ሥራዎችን በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢኒስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ውብአምላክ እሸቱ በበኩላቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢኒስቲቲዩት ጋር አብሮ ለመስራት ፈቃደኛ በመሆኑ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አያይዘውም ኢኒስቲቲዩቱ በዋናነት በሰራተኛው አቅም ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡