የሀገር ውስጥ ዜና

በሸካ ዞን በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

By Tibebu Kebede

June 17, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸካ ዞን በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባው የደገሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው ዕለት ተመርቋል።

በስነስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ዛሬ የተመረቀው የደገሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ተገንብተው የተመረቁ ትምህርት ቤቶችን ቁጥር 17 አድርሶታል።

በደቡብ ክልል የዛሬውን ጨምሮ ሶስት ትምህርት ቤቶች በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት መገንባታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ትምህርት ቤቱ ስምንት የመማሪያ ክፍሎች ያሉት ሲሆን በተጨማሪም ቤተ ሙከራ እና የአስተዳደር ብሎኮችን ያካተተ ነው።

ለትምህርት ቤቱ ግንባታ 10 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉ ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!