በስዊዘርላንድ በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ያልተገባ ጫናዎችን በመቃወም ሰልፍ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በኢትዮጵያ ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ያልተገቡ ጫናዎችን በመቃወም በጄኔቭ ከተማ ሰልፍ አካሂደዋል።
ሰልፈኞቹ ካስተጋቧቸው መልዕክቶች መካከል በኢትዮጵያ ላይ የምታሳድሩትን ያልተገባ ጫና አቁሙ፣ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘገባዎቻችሁ ሚዛናዊነትን የጠበቁ ይሁኑ፣ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፈን አንሰጥም የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡
በተጨማሪም የአሜሪካ መንግስት በሁለቱ ሃገራት መካከል ለዘመናት የዘለቀውን ወዳጅነት ታሳቢ በማድረግ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ለውጥ እንዲደግፍ እንዲሁም የሰብአዊ እርዳታ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ሰልፉን ያስተባበሩት የአውሮፓና ስዊዘርላንድ ‘ዲፌንድ ኢትዮጵያ’ ግብረ ሃይል አባላት ሲሆኑ፥ ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ ደብዳቤም በወቅቱ በስፍራው ለተገኙት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እንዲሁም ተቀማጭነታቸውን በጄኔቭ ከተማ ላደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ማስገባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share