Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ በ3ኛው የኮቪድ 19 ማዕበል ውስጥ ትገኛለች – የዓለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ በ3ኛው የኮቪድ19 ማዕበል ውስጥ እንደምትገኝ የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ፡፡

በዚህም ድርጅቱ ተጨማሪ ክትባት ለአህጉሪቱ እንደሚያስፈልግ አስታውቋል ፡፡

እስካሁን በአፍሪካ ከ5 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፥ ቢያንስ ሰባት የአፍሪካ ሃገራት መከላከያ ክትባት መጨረሳቸውም ነው የተነገረው፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ማትሺዲሶ ሞቲ “አፍሪካ ተጨማሪ ክትባቶችን ትፈልጋለች’’ ብለዋል ፡፡

ደቡብ አፍሪካ ፣ ሞሮኮ ፣ ቱኒዚያ ፣ ኢትዮጵያ እና ግብፅ በአህጉሪቱ በቫይረሱ በብዛት የተያዙ ሰዎች የሚገኝባቸው ሃገራት ናቸው፡፡

በኡጋንዳ እና ናሚቢያ በቫይረሱ ሳቢያ የበርካታ ዜጎቻቸው ህይዎት እያለፈ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው ፡፡

እስካሁን በአፍሪካ የ136 ሺህ 30 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ሳቢያ አልፏል፡፡

ዴልታ የተባለው የቫይረሱ ዝርያ በ14 የአፍሪካ ሀገራት የተገኘ ሲሆን፥ ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ የተገኘው የቤታ ዝርያ በ25 ሀገራት ውስጥ እንደሚገኝም ነው የተነገረው ፡፡

ድርጅቱ ተጨማሪ ክትባቶች መቼ እንደሚገኙ ግልጽ የሆነ የጊዜ ሰሌዳ እንደሌለ ጠቅሶ፥ ነገር ግን በተቻለ ፍጥነት አስቸኳይ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ለአፍሪካ እንደሚያስፈልግ ገልጿል ፡፡

ምንጭ ፥ ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.