ስፓርት

ጣሊያን፣ ቤልጂየም እና ኔዘርላንድስ በአውሮፓ ዋንጫ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል

By Tibebu Kebede

June 18, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ ቡድኖች እየተለዩ ነው፡፡

እስካሁን በተደረጉ ጨዋታዎች ከምድብ 1 ጣልያን፣ ከምድብ 2 ቤልጂየም እንዲሁም ከምድብ 3 ኔዘርላንድስ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል፡፡

ከምድብ 1 ጣሊያን ሁለት ጨዋታዎቿን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች፡፡

ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ ከምድብ 2 ቤልጂየም ዴንማርክን 2 ለ 1 አሸንፋለች፡፡

ቶርጋን ሃዛርድ እና ኬቪን ደ ብሩይነ የድል ጎሎቹን ለቤልጂየም ሲያስቆጥሩ፥ ፖልሰን የዴንማርክን ጎል አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ቤልጂየም ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋግጣለች፡፡

በምድብ 3 ከኦስትሪያ የተጫወተችው ኔዘርላንድስ በሜምፊስ ዲፓይ እና ደምፍራይስ ጎሎች 2 ለ 0 በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለች ሌላኛዋ ቡድን ሆናለች፡፡

በሌላኛው የምድቡ ጨዋታ ደግሞ ዩክሬን በያርሞሌንኮ እና ያሬምቹክ ሁለት ጎሎች መቄዶንያን 2 ለ 1 አሸንፋለች፡፡

የመቄዶንያን ማስተዛዘኛ ጎል ደግሞ አሊዮስኪ አስቆጥሯል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!