Fana: At a Speed of Life!

በሀገራዊ የሰላም ግንባታ ላይ የደህንነት እና የጸጥታ አካላት ዕይታ” በሚል ርዕስ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ጦር ኮሌጅ ከሰላም ሚኒስቴርና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “በሀገራዊ የሰላም ግንባታ ላይ የደህንነት እና የጸጥታ አካላት ዕይታ” በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት እያካሄደ ነው፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌና የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ፣ የክልል የፀጥታና የደህንነት አመራሮች ፣ ምሁራን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡
ውይይቱ በወቅታዊ ስትራቴጂክ የደህንነት እና የፀጥታ ጉዳዮች ላይ የጋራ አስተሳሰብ እንዲፈጠር ማድረግ እና የጦር ኮሌጅ ተማሪዎች በስትራቴጂክ የደህንነት ጉዳዮች ላይ ሁለንተናዊ አቅም እንዲያጎለብቱ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ታውቋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ውይይቱ ከሰላም ግንባታ ጋር የተያያዘ በመሆኑ የጋራ አቋም ለመያዝም ጠቃሚ መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.