Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ቶን የወጪና ገቢ እቃዎችን ማጓጓዙን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት አክሲዮን ማህበር ባለፉት ሶስት ዓመታት ከ3 ነጥብ 4 ሚሊየን ቶን በላይ የወጪና ገቢ ዕቃዎችን ማጓጓዙን አስታወቀ፡፡

የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጥላሁን ሰርካ እንደገለጹት፥ በመጀመሪያ ዓመት 800 ሺህ፣ በ2ኛ ዓመት 1 ነጥብ 2 ሚሊየን፣ በ3ኛ ዓመት 1 ነጥብ 45 ሚሊየን ቶን እቃ ማጓጓዝ ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ ባለፉት ሶስት ዓመታት ከ3 ነጥብ 45 ሚሊየን ቶን በላይ ዕቃ ማጓጓዙን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

በዚህም የወጪና ገቢ እቃዎች እድገት ማሳየቱን ጠቁመው፥ አገልግሎት አሰጣጡም በየአመቱ ከ25 እስከ 30 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱንና የሶስት ዓመታት ጉዞውም ስኬታማ እንደነበር አስታውቀዋል፡፡

የልማት መሳሪያዎች፣ የንግድ ሸቀጦች፣ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት አግልግሎት ድርጅትና የግሉ ዘርፍ በኮንቴነር የሚያስመጧቸውን ሸቀጦች በማጓጓዝም ስኬታማ እንደነበር አመልክተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.