Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ወጣቶች ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ወጣቶች ተናግረዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ወጣቶች የምርጫውን ውጤት በፀጋ መቀበል ከሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚጠበቅ እንደሆነም ነው የተናገሩት።
ወጣቶቹ ባወጡት የምርጫ ካርድም ይበጀናል ያሉትንና እንዲመራቸው የሚፈልጉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡
የምርጫ ካርድ ያወጣ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የምርጫ ካርዱን ድምፅ በመስጠት ዋጋ እንዲኖረው ማድረግ እንደሚገባውም ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር አካባቢያቸውን ነቅተው እየጠበቁ መሆኑን የተናገሩት ወጣቶቹ ይህንን ስራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል።
በመጨረሻም ሁሉም ማህበረሰብ በተለይም ወጣቱ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዙፋን ካሳሁን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.