Fana: At a Speed of Life!

ኪም ጆንግ ኡን ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ድርድርም ሆነ ለሚኖር ውጥረት ዝግጁ መሆን እንዳለባት ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ውይይትም ሆነ ለሚኖር ፍጥጫ ዝግጁ መሆን እንዳለባት ተናግረዋል፡፡

የሰሜን ኮሪያ ገዢው ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ በመዲናዋ ፒዮንግያንግ በተያዘው ሳምንት መካሄድ ጀምሯል፡፡

የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን በስብሰባው ላይ ሀገራቸው በቀጣይ ከአሜሪካ ጋር ለምታደርገው ውይይትም ሆነ ለሚኖር ፍጥጫ መዘጋጀት እንዳለባት ገልጸዋል፡፡

በተለይም ከኒውክሌር ጦር መሳሪያ እና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በሀገራቱ መካከል ለሚከሰት እሰጣ ገባ ፒዮንግያንግ ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ እድትሆን አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በኮሪያ ልሳነ ምድር ሊከሰት የሚችልን ማንኛውም ትንኮሳ ለመመከት እና ለመቆጣጠር መጠነ ሰፊ ዝግጀት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ይህም የሰሜን ኮሪያን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚደረግ ትግል ነው ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.