ወይዘሪት ሄራን ገርባ የ2021 ሲጋራ የማይጨስበት ቀን ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ የፈረንጆቹ 2021 ሲጋራ የማይጨስበት ቀን ሽልማት አሸናፊ ሆኑ፡፡
ሽልማቱ ዳይሬክተሯ በኢትዮጵያ ሲጋራ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ እንዳይጨስ የወጣውን መመሪያ በማስተግበርና በመቆጣጠር ላደረጉት አስተዋጽኦ እንደተበረከተላቸው የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመላክታል፡፡
ከእርሳቸው ቀደም ብሎ አራት ኢትዮጵያውያን ግለሰቦችና ድርጅቶች ይህን ሽልማት ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!