ከመተከል ዞን ተፈናቅለው በቻግኒ መጠለያ ካምፕ የነበሩ ነዋሪዎች ወደ ተዘጋጀላቸው መጠለያ መንቀሳቀስ ጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመተከል ዞን ተፈናቅለው በቻግኒ መጠለያ ካምፕ የነበሩ የማንቡክ እና የማንዱራ ወረዳ ነዋሪዎች ወደ ተዘጋጀላቸው የየወረዳቸው መጠለያ መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡
የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ ተመላሾቹ ወደ ቀያቸው ሲመለሱ ኮማንድ ፖስቱ የሚጠበቅበትን ለማድረግ ዝግጁ ነው ብለዋል።
የተፈናቀሉ ዜጎችን መመለስ የማይፈልጉ አንዳንድ አካላት መኖራቸውን የጠቆሙት ብርጋዴር ጄኔራል አለማየሁ፥ “ለእነዚህ አካላት አሉባልታና የሃሰት ወሬ ሳትበገሩ ወደ ተዘጋጀላችሁ ስፍራ ለመሄድ ያሳያችሁት ተነሳሽነት የሚደነቅ ነው” ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!