Fana: At a Speed of Life!

መራጮች አስፈላጊውን የኮቪድ 19 ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዜጎች ድምፅ ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በሚሄዱበት ወቅት አስፈላጊውን የኮቪድ 19 ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የምርጫ ቦርድ አሳሰቡ፡፡
ቦርዱ ለምርጫ አስፈፃሚዎች የኮቪድ 19 መከላከያዎች ማቅረቡን ገልፆ ህብረተሰቡ ግን የራሱን የመከላከያ ግብአቶች እንዲጠቀም ጠይቋል፡፡
ዜጎች ድምፅ በሚሰጡበት ወቅት የኮቪድ 19ን ታሳቢ ማድረግ እንዳለባቸው ደግሞ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል፡፡
መራጮች ድምፅ በሚሰጡበት ወቅት ርቀታቸውን መጠበቅ፣ የአፍና አፍንጫ ጭምብል ማድረግንና ንክኪ ስለሚኖር የእጅ ንፅናቸውን መጠበቅን መዘንጋት የለባቸውም ተብሏል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኮቪድ 19 ምላሽ አስተባባሪ አስቻለው አባይነህ መመሪያ 30ን በማክበር ራሳቸውን መጠበቅን ዜጎች መተግበር ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
ምክትል ዳይሬክተሩ ለዚህም ከምርጫ ቦርድ ጋር እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የምርጫ ቦርድ የኮሙዩኒኬሽን ሃላፊ ሶሊያና ሽመልስ ለምርጫ አስፈፃሚዎች የኮቪድ መከላከል ግብአቶች መሰራጨቱን ተናግረዋል፡፡
ለሁሉም ዜጎች የአፍና አፍንጫ ጭምብል ማቅረብ ባይቻልም በምርጫ ጣቢያዎች እጅ ማፅጃዎች መመቻቸታቸውን ሃላፊዋ ተናግረው ህብረተሰቡም ወደ የምርጫ ጣቢያዎች በሚሄድበት ጊዜ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.