Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ ሸዋ ዞን ነዋሪዎች በአጣየና አካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ነዋሪዎች በአጣየና አካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ1ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ነዋሪዎቹን ወክለው 400 ኩንታል የዕለት ደራሽ የምግብ ግብአት ለሰሜን ሸዋ ዞን ያስረከቡት አባገዳዎችና የሃገር ሽማግሌዎች ሲሆኑ÷ የወንድሞቻችን ጉዳት የኛ ጉዳት ነው ብለዋል።

አባገዳ ቱፋ ጅሩ እኛ ተዋደን የምንኖር እንጂ ሰላማችንን ለማደፍረስ የሚሰሩ ሃይሎች በቀላሉ የሚለዩን አይደለንም ነው ያሉት።

ከዚህ የዕለት ደራሽ ድጋፍ በተጨማሪ 100ሺህ ብር ድጋፍም ለዞኑ አስተዳደር አስረክበዋል።

የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ጠንካራ ትስስር ያለው በመሆኑ በወንድሞቻችን ጉዳት ተጎድተናል ያሉ ሲሆን÷ ለዚህም ነው ህዝቡ ፍቅሩን በድጋፍ ያሳየው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረ ፃድቅ የምስራቅ ሸዋ ዞን ነዋሪዎችን አመስግነዋል።

በሳምራዊት የስጋት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.