የሀገር ውስጥ ዜና

የቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት የቦርሳ እና ጫማ ስጦታዎችን ለተማሪዎች አበረከተ

By Meseret Awoke

June 18, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት የቦርሳ እና ጫማ ስጦታዎችን ለተማሪዎች አበርክቷል፡፡

ፅህፈት ቤቱ ከዚህ ቀደም የሚያደርገውን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በመቀጠል የቦርሳ እና ጫማ ስጦታዎችን ባስገነባቸው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች እና በአካባቢው ለሚገኙ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በስጦታ አበርክቷል፡፡

ስጦታውን ከተረከቡ አካባቢዎች መካከል ደቡብ ወሎ ጦሳ ፈላና፣ ደባርቅ፣ ሸካ ዞን ማሻ ወረዳ እና አጋሮ እንደሚገኙበት ከጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!